በገዳሙና በቤተ ክርስቲያኑ ያሉ ታቦታት

መንፈስ ቅዱስ

ስለ ገዳሙ

ቅድስት አርሴማ

ስለ ገዳሙ

አቡነ ኪሮስ

ስለ ገዳሙ
መንፈስ ቅዱስ ማን ነው?

መንፈስ ቅዱስ ማን ነው? ለሚለው ጥያቄ ብዙዎች የተለያየ ግንዛቤ አላቸው፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንደ ረቂቅ ኃይል ይመለከቱታል፡፡ ሌሎች ደግሞ  እግዚአብሔር ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ የገለጠውና ማንነት የሌለው ኃይል እንደሆነ ይረዳሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር እንደሆነ ያውጃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም  አእምሮ ያለው ማንነት፤ ስሜትና ፈቃድ ያለው መለኮታዊ አካል እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ቅዱስ ባስልዮስ «እኔ እግዚአብሔር በምልበት ጊዜ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለቴ ነው» ብሎ እንደተናገረው እግዚአብሔር የሚለው ስም የሥላሴ መጠሪያ ነው፡፡ የአብ የወልድ እስትንፋሳቸው የሆነ መንፈስ ቅዱስም ከአብ ከወልድ ጋር በዕሪና በፍጹም መተካከል ያለ ነውና እግዚአብሔር መሆኑን እንመሠክራለን፡፡ ይኽውም የቅዱሳን ነቢያት ሐዋርያትና መምህራን ትምህርት ምስክር ነው፡፡

ስለ ገዳሙ አመሠራረት

በምስረታው አላማላይ እንደተገለጠ በፈቃደ እግዚአብሔር ቢመሰረትም የመስራቹ ካህን አላማና ፍላጎት ከከተማ ወጣ ያለ ጸጥታና ሰላም የሚሰማበት የጽሞና የአርምሞ ሰላማዊ የጸሎት ስፍራ ማዘጋጀት በልዩ ልዩ ጭንቀት ሰላም በማጣት በህመም እንዲሁም በሐዘን ላሉ በካናዳ ና በመላው የአሜሪካ ግዛት ለሚገኙ ምእመናን መጽናኛ የጸበል መጠመቂያ ስፍራ ማዘጋጀት ስለነበረ ከመጀመርያው ጀምሮ አብረው ሲያገለግሉ የነበሩ መስራች አባላትም መስራቹ ካህን ያቀረቡትን ይህንን ትልቅ ሀሳብና ራዕይ ለመፈጸም በጸሎት በበጎ ሀሳብ በእውቀትና በገንዘብ እንዲሁም በጉልበት በቅንነት ከስኬት ለማድረስ እየተጉ ይገኛሉ።

ከላይ እንደተገለጠው ቦታው የጸሎት የሱባኤ የጽሞናና የአርምሞ ስፍራ ሆኖ ቅዳሴ በዓመት ሁለቴ ብቻ ለክብረበዓል የሚቀደስበት እንዲሆን የታሰበ ሲሆን ስፍራው በብዕፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ከ ሐምሌ 28 / 2010 ዓ . ም ጀምሮ በርካታ ምእመናን ከአውሮፖ ከካናዳና ከመላው አሜሪካ ደውለው ሳይመዘገቡ ና ሳያሳውቁ ወደስፍራው በማቅናት በገዳሙም አካባቢ ካሉ እስቴቶች ምእመናን በየጊዜው በመምጣት በመጸለይ ስእለት በመሳል የታመሙት በተአምራት እየተፈወሱ ስራያጡ ስራ እያገኙ ለረጅም ዓመት በትዳር የነበሩና ልጅ ያልነበራቸው ልጅ እያገኙ ትዳር ያጡ የትዳር አጋር እያገኙ ስለታቸውን ለመፈጸም የወለዱት ተስለን ልጅ አግኝተናልና ክርስትና አንሱልን የትዳር አጋር ያገኙት ስዕለት ሰምሯልና በተክሊል በቁርባን አጋቡን ሌሎችም ተስለን ለንስኃ ለቁርባን በቅተናልና አቁርቡን እያሉ ጥያቄ በማቅረባቸው ምክንያት በአቅራቢያው ያሉ ለጸበልና መንፈሳቸውን ለማሳረፍ ወደቦታው ቤተሰቦቻቸውን በሙሉ ሰብስበው ስንቅ ቋጥረው ጸልየው ተጠምቀው ጸበላቸውን ጠጥተው ውለው የሚሄዱ በርካቶች ስለሆኑ ከሰው ብዛት የተነሳ እንደታሰበው የጽሞናና የጸጥታ ስፍራ ሆኖ የመቀጠሉ ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ስለገባ ቦታውን ለሁለት ከፍሎ አንዱን ስፍራ ከልሎ ቤተክርስቲያን አድርጎ ክርስትና ለማንሳት የጋብቻ ስርአት ለመፈጸም ለሚቆርቡት ስረአተ ቁርባን ለመፈጸም እለታዊ ወራሐዊና አመታዊውን አገልግሎት ለመስጠት ከነቤተሰቦቻቸው ውለው ለመመለስ ለሚመጡ ደርሰው ተሳልመውና ጸልየው ለሚመለሱ በመንፈስ ቅድሰ ስም በሚታነጸው ቤተክርስቲያን አገልግሎቱን እንዲሰጥ ለማስቻል ሱባኤ ገብተው በአርምሞና በጽሞና ቆይተው ለመሔድ ለሚፈልጊ ብቻ የገዳሙን ስፍራ ከልሎ የገዳምነት መንፈሱን ጠብቆ ለሱባኤ ለአርምሞና ለጽሞና የሚመች ከትውልድ ወደትውልድ እንዲተላለፍ አድርጎ ለመጠበቅ የጸጥታ ስፍራ ለማድረግ የወደፊት እድገቱን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ለማዘጋጀት በመስራቹ ካህን በመጋቤ ሃይማኖት ተስፋዬ ሙቆያ አቅራቢነት ና አሳሳቢነት መስራች አባላቱ እና አስተዳደር ኮሚቴው አውቆት በአገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ተቀባይነት አግኝቶና ጸድቆ ጽራሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያንና የምእራፈ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ የአንድነት ገዳም ተብሎ ተሰይሟል።

ስለሆነም ከላይ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች የተነሳ ወደፊትም የታቀዱትን ትልልቅ እቅዶች ባገናዘበመልኩ በመንፈስ ቅዱስና በቅድስት አርሴማ ስም ቤተክርስቲያንና ገዳም ተብሎ ተመስርቷል ስያሜም አግኝቷል::

የገዳሙ መስራች ካህን

በሜሪላንድ የጽርሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን እና የምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም መስራችና አስተዳዳሪ ፤ የዋሽንግተን ዲሲ አና አካባቢው  ሀገረ ስብከት የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ክፍል ሀላፊ ፤ በዋሽንግተን ዲሲ ርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለ14 አመታት በስብከተ ወንጌል ክፍል ሀላፊ ያገለገሉ፣

መልአከ መዊዕ ተስፋዬ መቆያ

በሜሪላንድ የጽርሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን እና የምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም መስራችና አስተዳዳሪ ፤ የዋሽንግተን ዲሲ አና አካባቢው ሀገረ ስብከት የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ክፍል ሀላፊ ፤ በዋሽንግተን ዲሲ ርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለ14 አመታት በስብከተ ወንጌል ክፍል ሀላፊ ያገለገሉ፣

የገዳሙ አበምኔት (2018 - 2024)

መላከ ሰላም ቆሞስ አባ ገብረማሪያም

መላከ ሰላም ቆሞስ አባ ገብረማሪያም

ገዳሙን የባረኩ

የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው  ሃገረ ስብክት ሊቀዻዻስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ጽርሃ ጽዮን መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ እና ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ የአንድነት ገዳምን ለመጀመሪያ ጊዜ መስከረም 11 ቀን 2010 ዓ/ም (September 21, 2017) ባረኩ

ብጹእ አቡነ ፋኑኤል

የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሃገረ ስብክት ሊቀዻዻስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ጽርሃ ጽዮን መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ እና ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ የአንድነት ገዳምን ለመጀመሪያ ጊዜ መስከረም 11 ቀን 2010 ዓ/ም (September 21, 2017) ባረኩ

የገዳሙና የቤተ ክርስቲያኑን የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጡ ሊቃነ ጳጳሳት

ብጹዕ አቡነ ሕርያቆስ

ብጹዕ አቡነ ሕርያቆስ

ብጹዕ  አቡነ ሳዊሮስ

ብጹዕ  አቡነ ሳዊሮስ

ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል

ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል

 

 

 

 

 

 

 

ገዳሙን እና ቤተ ክርስቲያኑን በተለያየ ጊዜ ተገኝተው የባረኩ ብጹዐን አባቶች

ብፁዕ አቡነ ያሬድ

ብፁዕ አቡነ ያሬድ

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ

ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ

ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል

ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ

ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ

ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ

ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ

ብፁዕ አቡነ ሩፍኤል

ብፁዕ አቡነ ሩፍኤል

ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ

ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ

ብፁዕ አቡነ በርናባስ

ብፁዕ አቡነ በርናባስ

ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ

ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል