የገዳሙ አገልግሎት እና ስርአት
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
እንኳንወደ ጽርሃ ጽዮን መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን እና ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ የአንድነት ገዳም በሰላም መጡ። ቆይታዎ የተሳካ እና ሱባኤዎ የሰመረ እንዲሆን እየተመኘን በቆይታዎ ጊዜ ማድረግ ስለሚገዎ እና ስለማይገዎ ተግባራት በዚህ መመሪያ ውስጥ ተካቷዋል። በተጨማሪ ከዚህ መመሪያ ውስጥ ያልተካተቱ ጥያቄዎች ቢኖርዎት በቤተክርስቲያኑ ወይም በገዳሙ ለዚህ ጉዳይ የተመደቡትን አገልጋዮች ያነጋግሩ።
በቤተክርስቲያኑ ወይም በገዳሙ የሚሰጠው የጸበል ፣ የሱባኤ ወይም ሌሎች አግልግሎቶች የስርዓተ አምልኮቱ አካል ስለሆኑ በምዕመናን/ ተገልጋዮች ነፃ እና ሙሉ ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው።
ስለዚህ በቆይታዎ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች በቀና መንፈስ እና በባለቤትነት ስሜት እንዲተገብሩ እየገለፅን
መመሪያዎቹን መተግበር መንፈሳዊ ግዴታ መሆኑን በአፅንኦት እናሳስባለን ።
የገዳሙ አገልግሎት
ክርስትና ማስነሳት
ጸሎተ ቀንዲል
የጋብቻና የቁርባን ትምህርት
የምክር አገልግሎት
ጋብቻ መፈፀም
ጸሎተ ፍትሐት
ጸበል መጠመቅ
ሱባኤ መግባት
የቄደር ጥምቀት
በጸሎት መታሰብ ለሚፈልጉ ምዕመናን መመዝገቢያ ቅፅ
ለጸበል ወይም ለሱባኤ የሚመጡ ምዕመናን መመዝገቢያ ቅፅ
ክርስትና ማስነሳት ለሚፈልጉ ምዕመናን መመዝገቢያ ቅፅ
ጋብቻ መፈፀም ለሚፈልጉ ምዕመናን መመዝገቢያ ቅፅ
የቄደር ጥምቀት ለሚፈልጉ ምዕመናን መመዝገቢያ ቅፅ
ጸሎተ ቀንዲል ለሚፈልጉ ምዕመናን መመዝገቢያ ቅፅ
የቄደር ጥምቅት
- ቄደር የንስሐ እጽበት ነው፤ ያደፈ ልብስ እነደሚታጠብ ሁሉ ይህም ሰው ንጽሕት እምነቱን አሳድፏልና ከኃጢያቱ ለመታጠቡ ምልክት ይሆን ዘንድ በማየ ጸሎት ይታጠባል፡፡
- በዓረብኛ ቀድር ይባላል፤ ትርጉሙም እድፍ ርኩስ ማለት ነው፤ መጽሐፉ ወደ ግዕዝ ከተተረጎመ በኃላ ቄደር ተብሏል፡፡
- በአሕመድ ግራኝ ወረራ ጊዜ በ፲፮ቱ ዓመታት በተቆጣጠረው ቦታ ሁሉ የሚኖር ትልቅም ይሁን ትንሽ ካልሰለመ ለመኖር አይችልም ነበር፡፡
- ከዚህም የተነሳ ብዙ ሕዝብ ሰልሟል፤ የሰለመውን ሕዝብ እንደገና ወደ ክርስትና ለመመለስ ገላውዴዎስ መጽሐፍ ቄደርን ከዓረበኛ ወደ ግዕዝ አስተረጉመውታል፡፡
- ቄደር የንስሐ ጸሎት ማለት ነው፤ አንዳንድ መምህራን ቄደርን ከዮሐንስ ጥምቀት ጋር ያያይዙታል፤ የዮሐንስ የንስሐ እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሷል፤ ስለዚህም ነው የቄደር ጥምቀት ከዮሐንስ ጥምቀት ጋር የሚያያዙት፡፡
- በቤተ ክርስቲያን ስደት ከተጀመረ አንስቶ ስደት ፈርተው ከሃይማኖታቸው የወጡትን ሁሉ ለመመለስ የቤተክርስቲያን አባቶች ይህን መጽሐፍ አዘጋጅተዋል፡፡
- የመጽሐፉ መጀመሪያም “መጽሐፈ ቄደር” ሃይማኖቱን ለካደ ወይም ላረከሰ ወንድም ይሁን ሴት የወንድ መነኩሴም ይሁን የሴት መነኩሲት የቤተክርስቲያን መምህራን ያዘጋጁት ነው፡፡
- የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በዚሁ መጽሐፍ ተጠቅማ የጠፉትን በጎቿን መልሳለች፡፡ በመጽሐፉ የሰፈረው ጸሎት ይደገምና ውሃው በተመለሱት ሰዎች ላይ ይረጫል ወይም ይጠመቁታል፡፡
ጸሎተ ቀንዲል
ሚስጥር ቀንዲል በካህኑ ጸሎት እና ቡራኬ በሽተኛው ሰውዬ በተባረከው ዘይት በመቀባቱ ከበሽታው መዳንን ከኃጢያት መንፃትን የሚያስገኝ ምስጢር ነው፡፡ ይኸውም ምስጢር ለአካለ ስጋም ለአካለ ነፍስም ጤንነትን ለመስጠት የእግዚአብሔር ጸጋንም ለማስተላለፍ የሚችል ነው፡፡ ቀንዲል ማለት መብራት ማለት ነው፡፡ ሚስጢረ ቀንዲል በሚደረግበት ጊዜ መብራት ይበራል ስለዚህም ስያሜው ከስርዓቱ አፈጻጸም ተወስዷል(ዘፍ ፵፡፬ ዘኁሉ ፬፡፱)፡፡
ይህንን ምስጢር የመሰረተው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ አስራሁለቱን ሐዋርያት ጠርቶ ስልጣንን በሰጣቸው ጊዜ የመፈወስ ስልጣን ሰጥቷቸዋል(ማቴ ፲፡፩ ማር ፮፡፯ ሉቃ ፱፡፩)፡፡ “በወጡ ጊዜም አስተምሮ ንስሐ ይገቡ ዘንድ እጅግም ሰይጣናትን አውጡ በዘይትም ብዙ ድውያንን ቀቡ አድኗቸውም” (ማር ፮፡፲፪-፲፫)፡፡ ከትንሳኤ በኋላ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውይ የመፈወስ ሃይል ሰጥቷቸዋል፡፡(ማቴ ፮፡፲፯-፲፰) ሐዋርያትም ሚስጥር መጋቢዎች እንደመሆናቸው በትእዛዙ መሰረት ሲሰሩበት ኖረዋለ(፩ኛ ቆሮ ፬፡፩)፡፡ ቀጥሎ ቀሳውስቱን በዘይት እየቀቡና እየፀለዩ ህሙማኑን እንዲፈውሱ ሐዋርያት አዘዋል፡፡ “ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተክርስቲያን
ቀሳውስትን ወደ እርሱ ይጥራ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት የእምነት ጸሎት ድውይን ያድናል፤ ጌታም ያስነሳዋል ኃጢያትም ሰርቶ እንደሆን ይሰረይለታል” (ያዕ ፭፡፲፬-፲፭) ቤተክርስቲያን ይህን ቅዱስ ምስጢር ሲወርድ በመጣው ትውፊት መሰረት ሰትፈጽመው ትኖራለች በመፈጸምም ላይ ትገኛለች፡፡
ምስጢረ ቀንዲል የሚፈጸመው ከንጹህ የወይራ ዘይት ነው። ቅብዐ ቅዱስ እየተባለ ይጠራል። ማንም ሰው በማንኛውም ጊዜ ሲታመም ካህኑን ጠርቶ ምስጢረ ቀንዲል ሊጠይቅና ሊፈጸምለት ይችላል። ቅባ ቅዱሱን ጳጳስ ይባርካል። ምስጢረ ቀንዲል በቤተክርስቲያን፣ በመኖሪያ ቤት እና በሆስፒታል ሊፈጸም ይችላል። በሽተኛው ከመቀባቱ በፊት ኃጢያቱን ይናዘዛል ከዚያም ዘይቱ ቀርቦ ሥርአተ ጸሎቱ ይፈጸማል። በመቀጠል ካህኑ በሽተኛውን በጭንቅላቱ ላይ እጁን ጭኖ ይጸልያል በመጨረሻም አምስቱን ህዋሳት ማለት አይኑን፣ አፉን፣ ጆሮውን፣ አፍንጫውን እና እጁን ይቀባል። በዐይኑ አይቶ፣ በአንፍጫው አሽትቶ፣ በጆሮው ሰምቶ፣ በአፉ ተጋግሮ፣ በእጁ ዳሶ ለሰራው ኃጢያት ስርየት እንዲሆንለት ሲል ነው። በዚህ ጊዜ በሽተኛው በሥጋ ደዌ ደክሞ የነበረው መንፈሳዊ በሽተኛው ሥርየት ያገኛል። በዚህ በሚታየው ምሥጢር የማይታይ ፀጋ ይገኝበታል።
የገዳሙ ስርአት እና መመሪያ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
እንኳንወደ ጽርሃ ጽዮን መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን እና ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ የአንድነት ገዳም በሰላም መጡ። ቆይታዎ የተሳካ እና ሱባኤዎ የሰመረ እንዲሆን እየተመኘን በቆይታዎ ጊዜ ማድረግ ስለሚገዎ እና ስለማይገዎ ተግባራት በዚህ መመሪያ ውስጥ ተካቷዋል። በተጨማሪ ከዚህ መመሪያ ውስጥ ያልተካተቱ ጥያቄዎች ቢኖርዎት በቤተክርስቲያኑ ወይም በገዳሙ ለዚህ ጉዳይ የተመደቡትን አገልጋዮች ያነጋግሩ።
በቤተክርስቲያኑ ወይም በገዳሙ የሚሰጠው የጸበል ፣ የሱባኤ ወይም ሌሎች አግልግሎቶች የስርዓተ አምልኮቱ አካል ስለሆኑ በምዕመናን/ ተገልጋዮች ነፃ እና ሙሉ ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው።
ስለዚህ በቆይታዎ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች በቀና መንፈስ እና በባለቤትነት ስሜት እንዲተገብሩ እየገለፅንመመሪያዎቹን መተግበር መንፈሳዊ ግዴታ መሆኑን በአፅንኦት እናሳስባለን ።