መንፈስ ቅዱስ

IMG_FED18C4B954A-1

ቅድስት አርሴማ

IMG_2984
ቅድስት አርሴማ ማናት?

እንኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሌን ተሸክሞ ይከተለኝ፤…ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢገዛ ፍሱንም ቢያጎድል
ምን ይተቅመዋል?ተብሎ የተነገረውን የክርስቶስ ወንጌል ተከትላ፡ ዘመድ አዝማዶቿን ትታ፤ጌታን የተከተለች፤ በሮምና
በአርማንያ ገዥዎች የነበሩ ሁለት ከህዲያን ነገሥታት ዲዮቅልጥያኖስንና ድርጣድስን፤ በሃይማኖቷ ጸንታ ድል ያደረግች፤
የሮም ወታደሮች የሚያደርሱባት መከራና ግፍ፤ አስራትና ግርፋት ያልበገራት በዘመኑ ከርሳሷ ጋር ከነበሩ መላ ሕይወታቸውን
ለእሳትና ለስለት ከሰጡት ከ27ቱ ቅዱሳት ደናግል አንዷ ሰማዕት ቅድስ አርሴማ ናት።

ስለ ገዳሙ ኣመሰራረት

በምስረታው አላማላይ እንደተገለጠ በፈቃደ እግዚአብሔር ቢመሰረትም የመስራቹ ካህን አላማና ፍላጎት ከከተማ ወጣ ያለ ጸጥታና ሰላም የሚሰማበት የጽሞና የአርምሞ ሰላማዊ የጸሎት ስፍራ ማዘጋጀት በልዩ ልዩ ጭንቀት ሰላም በማጣት በህመም እንዲሁም በሐዘን ላሉ በካናዳ ና በመላው የአሜሪካ ግዛት ለሚገኙ ምእመናን መጽናኛ የጸበል መጠመቂያ ስፍራ ማዘጋጀት ስለነበረ ከመጀመርያው ጀምሮ አብረው ሲያገለግሉ የነበሩ መስራች አባላትም መስራቹ ካህን ያቀረቡትን ይህንን ትልቅ ሀሳብና ራዕይ ለመፈጸም በጸሎት በበጎ ሀሳብ በእውቀትና በገንዘብ እንዲሁም በጉልበት በቅንነት ከስኬት ለማድረስ እየተጉ ይገኛሉ።

ከላይ እንደተገለጠው ቦታው የጸሎት የሱባኤ የጽሞናና የአርምሞ ስፍራ ሆኖ ቅዳሴ በዓመት ሁለቴ ብቻ ለክብረበዓል የሚቀደስበት እንዲሆን የታሰበ ሲሆን ስፍራው በብዕፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ከ ሐምሌ 28 / 2010 ዓ . ም ጀምሮ በርካታ ምእመናን ከአውሮፖ ከካናዳና ከመላው አሜሪካ ደውለው ሳይመዘገቡ ና ሳያሳውቁ ወደስፍራው በማቅናት በገዳሙም አካባቢ ካሉ እስቴቶች ምእመናን በየጊዜው በመምጣት በመጸለይ ስእለት በመሳል የታመሙት በተአምራት እየተፈወሱ ስራያጡ ስራ እያገኙ ለረጅም ዓመት በትዳር የነበሩና ልጅ ያልነበራቸው ልጅ እያገኙ ትዳር ያጡ የትዳር አጋር እያገኙ ስለታቸውን ለመፈጸም የወለዱት ተስለን ልጅ አግኝተናልና ክርስትና አንሱልን የትዳር አጋር ያገኙት ስዕለት ሰምሯልና በተክሊል በቁርባን አጋቡን ሌሎችም ተስለን ለንስኃ ለቁርባን በቅተናልና አቁርቡን እያሉ ጥያቄ በማቅረባቸው ምክንያት በአቅራቢያው ያሉ ለጸበልና መንፈሳቸውን ለማሳረፍ ወደቦታው ቤተሰቦቻቸውን በሙሉ ሰብስበው ስንቅ ቋጥረው ጸልየው ተጠምቀው ጸበላቸውን ጠጥተው ውለው የሚሄዱ በርካቶች ስለሆኑ ከሰው ብዛት የተነሳ እንደታሰበው የጽሞናና የጸጥታ ስፍራ ሆኖ የመቀጠሉ ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ስለገባ ቦታውን ለሁለት ከፍሎ አንዱን ስፍራ ከልሎ ቤተክርስቲያን አድርጎ ክርስትና ለማንሳት የጋብቻ ስርአት ለመፈጸም ለሚቆርቡት ስረአተ ቁርባን ለመፈጸም እለታዊ ወራሐዊና አመታዊውን አገልግሎት ለመስጠት ከነቤተሰቦቻቸው ውለው ለመመለስ ለሚመጡ ደርሰው ተሳልመውና ጸልየው ለሚመለሱ በመንፈስ ቅድሰ ስም በሚታነጸው ቤተክርስቲያን አገልግሎቱን እንዲሰጥ ለማስቻል ሱባኤ ገብተው በአርምሞና በጽሞና ቆይተው ለመሔድ ለሚፈልጊ ብቻ የገዳሙን ስፍራ ከልሎ የገዳምነት መንፈሱን ጠብቆ ለሱባኤ ለአርምሞና ለጽሞና የሚመች ከትውልድ ወደትውልድ እንዲተላለፍ አድርጎ ለመጠበቅ የጸጥታ ስፍራ ለማድረግ የወደፊት እድገቱን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ለማዘጋጀት በመስራቹ ካህን በመጋቤ ሃይማኖት ተስፋዬ ሙቆያ አቅራቢነት ና አሳሳቢነት መስራች አባላቱ እና አስተዳደር ኮሚቴው አውቆት በአገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ተቀባይነት አግኝቶና ጸድቆ ጽራሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያንና የምእራፈ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ የአንድነት ገዳም ተብሎ ተሰይሟል።

ስለሆነም ከላይ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች የተነሳ ወደፊትም የታቀዱትን ትልልቅ እቅዶች ባገናዘበመልኩ በመንፈስ ቅዱስና በቅድስት አርሴማ ስም ቤተክርስቲያንና ገዳም ተብሎ ተመስርቷል ስያሜም አግኝቷል::

የገዳሙ መስራች ካህን

በርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን የስብከተ ወንጌል ክፍል ሀላፊ፣ የዋሽንግተን ዲሲ አና አካባቢው  ሀገረ ስብከት የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ክፍል ሀላፊ

መጋቤ ሃይማኖት ተስፋዬ መቆያ

በርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን የስብከተ ወንጌል ክፍል ሀላፊ፣ የዋሽንግተን ዲሲ አና አካባቢው ሀገረ ስብከት የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ክፍል ሀላፊ

የገዳሙ አበምኔት

መላከ ሰላም ቆሞስ አባ ገብረማሪያም ግሩም

መላከ ሰላም ቆሞስ አባ ገብረማሪያም ግሩም

ገዳሙን የባረኩ

የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው  ሃገረ ስብክት ሊቀዻዻስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ጽርሃ ጽዮን መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ እና ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ የአንድነት ገዳምን ለመጀመሪያ ጊዜ መስከረም 11 ቀን 2010 ዓ/ም (September 21, 2017) ባረኩ

ብጹእ አቡነ ፋኑኤል

የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሃገረ ስብክት ሊቀዻዻስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ጽርሃ ጽዮን መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ እና ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ የአንድነት ገዳምን ለመጀመሪያ ጊዜ መስከረም 11 ቀን 2010 ዓ/ም (September 21, 2017) ባረኩ

በገዳሙ የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጡ ሊቃነ ጳጳሳት

photo_2022-07-07_02-44-00
IMG_5765

ብጹዕ አቡነ ሕርያቆስ

የከምባታ ሀዲያ ሊቀ ጳጳስ የቅድስ ሲኖዶስ አባል

 

IMG_0483

ብጹዕ  አቡነ ሳዊሮስ

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስ ሲኖዶስ አባል

 

IMG_1443

ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል

የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሃገረ ስብክት ሊቀዻዻስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል